የብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን አባልና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰላም ግንባታና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢኒየም መንገሻ በስነ ሰርዓቱ ላይ እንደተናገሩት ሰምምነቱ ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን በመናበብ መታገል እንደሚያስችል ገልፀው፤ ይህም በተዋረድ ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡ አክለውም የመግባቢያ ሰነዱ ብልፅግና ፓርቲ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ያለውን ዝግጁነት የሚያሳይ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡
ሰነዱን ያቀረቡት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የኢንስቴክሽንና ሥነ – ምግባር ኮሚሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ስንታየሁ አበበ በበኩላቸው ሁለቱ ተቋማት በስልጠና፣ ሙስና ለመከላከል በሚረዱ መረጃዎች ልውውጥና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ አብረው እንደሚሰሩ አስረድተዋል፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ከማል ሀሰን በበኩላቸው ስምምነቱ የኮሚሽኑን ተልዕኮ ለማሳካት አንድ እርምጃ የቀደመ መሆኑን ገልፀዋል።
በፊርማ ስነ ስርዓቱ የርዕሰ መስተዳድርና የካቢኒ ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሸሪፍ ሃጅአኑርን ጨምሮ የፍትህ ተቋማት አመራሮችና ባለድርሻዎች ተገኝተዋል።

