ሙስናን በመታገል ከሀገርና ህዝብ ላይ የሚደርሰውን አሉታዊ ተዕጽኖ ቀድሞ መከላከል የሁሉም ተግባር መሆን እንደሚገባ ተገለፀ።

-

(ፓዊ:-ነሀሴ 25/2014 ዓ.ም) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ለፓዊ ወረዳ አመራሮች እና ለስነ-ምግባር መኮነኖች በስነ-ምግባራዊ አመራር ምንነት፣ አስፈላጊነት፣ መርሆችና ተግዳሮቶች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል።

በስልጠናውም አመራሩና ፈጻሚ አካላት የወከላቸውን ህዝብ ከሌብነትና ከሙስና አስተሳሰብ ተግባር ፀድተው በግልጸኝነት፣ በፍትሃዊነትና በተጠያቂነት መርህ ለማህበረሰቡ ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል እንደሆነም በስልጠናው ተገልጿል።

በተላይ የህዝብን ጥቅም ወደ ጎን በመተው የራሱን ጥቅም ለማበልፀግ ከስራ ቅጥርና ምደባ፣ ከግዥ ስርዓት፣ ማህበራዊ መሠረተ ልማት ተቋማት ግንባታ፣ በንግድ፣ ትራንስፖርት እና በሌሎች ዘርፎች የሚስተዋሉ የሙስና ወንጀሎችን ለመከላከል የሚደረገውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ ማስቀጠልና በድርጊቱ ተሳትፈው የተገኙ አካላት ላይ ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ ኮሚሽኑ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪም በወረዳ ደረጃ የተቋቋሙ የስነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች ስራቸውን በአግባቡ እንዲወጡ የወረዳ አመራሩና ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጭምር ተጠቁሟል።

ተሳታፊ አመራሮችም በስነ-ምግባርና ጸረ- ሙስና ኮሚሽኑ ለወረዳ አመራሩ የተሰጣቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ቀጣይ ለሚከናወኑት ተግባራት አጋዥ መሆኑን ጠቅሰው ስልጠናዉ በወረዳው ለሚገኙ መንግስታዊ ተቋማትና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም ለባለድርሻ አካላት በተመሳሳይ ቢሰጥ ይበልጥ ሙስናን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት የሚያጠናክር መሆኑን ገልፀዋል ሲል የዘገበው የመተከል ዞን ፓዊ ወረዳ መንግስት ኮምዩኒኬሽን ጽ/ቤት ነው፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *