የትብብር ሰነዱ ሁለቱ ተቋማት በጋራ በመስራት እንደ ክልልና እንደ ሃገር የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የሚያግዝ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
በሰነዱ በስነ-ምግባር ግንባታ፣ ሙስና መከላከልና መልካም አስተዳደር ስልጠና፣ በኮምዩኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ስራዎች፣ የአይሲቲ ውጤቶች አጠቃቀም፣ አሰራርና አደረጃጀቶች፣ ወቅታዊ እና አስፈላጊ የሆኑ ሙያዊ የምክር አገልግሎቶች እንዲሁም ሌሎች በሁለቱ ተቋማት ፍላጎቶች መሰረት ባደረጉ ጉዳዮች በትብብር እንደሚሰራ ሰነዱን ያቀረቡት አቶ ባዛብህ አበጀሁ (በኮሚሽኑ የአውታሮች ኬዝ ቲም አስተባባሪ) አመላክተዋል፡፡
የስምምነቱን አስፈላጊነት የገለፁት ኮሚሽነር መንግስቱ ላሎ ሙስናን ከሌሎች ተቋማት ጋር በቅንጅት በመከላከል ትግሉ ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረው ማድረግ እንደሚያስፈለግ ገልፀዋል፡፡
አቶ ኦሳማ ከሊፋ (የክልሉ ወሳኝ ኩነት ዋና ዳይሬክተር) በበኩላቸው በወሳኝ ኩነት ሰነዶች የሚፈፀም ሙስና ስር እየሰደደ መሆኑን ጠቁመው በአግባቡ መከላከል ካልተቻለ በሃገርና በህዝብ ላይ ከፍተኛ ኪሳራን እንደሚያስከትል አስገንዝበዋል፡፡ በዚህ ዘርፍ የሚስተዋሉ የሙስና ተግባራትንም በጋራ በመስራት መከላከል እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡
ሃሳብ አስተያዬታቸውን የሰጡት ተሳታፊዎች ከስምምነት ሰነዱ በኋላ ጠንከር ያሉ ስራዎች በጋራ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
የሥምምነት ሰነዱ በክልሉ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በኩል መንግስቱ ላሎ (ኮሚሽነር) በክልሉ ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ በኩል ድግሞ አቶ ኦሳማ ካሊፋ (የክልሉ ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር) በአሶሳ ከተማ ተፈርሟል፡፡
በዚሁ መድረክ አቶ ሽመልስ ለገሰ (የክልል ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የትምህርትና ስልጣና) የወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የሚሰራቸውን ስራዎች እና ተልዕኮውን በሚመለከት ሰነድ አቅርበው ለታሳታፊዎች ግንዛቤ ፈጥረዋል፡፡
መድረኩን የመሩት አቶ ሰይድ ባብከር (የቤ/ጉ/ክ/መ ጠቅላይ አቃቤ/ዋና አቃቤ ህግ እና የኤጀንሲው የቦርድ ሰብሳቢ) እና አቶ ብርሃን አየሁ (የቤ/ጉ/ክ/መ ጠቅላይ ዐቃቤ ም/ አቃቤ ህግ) ናቸው፡፡




You, Mengistu Lalo, Yilma Tilahun and 23 others
