(ባምባሲ፤21/2015 ዓ.ም) በቅንጅትና በትብብር ከሰራን በፀረ-ሙስና ትግሉ የሚፈለገው ውጤት ላይ እንደርሳለን ሲሉ ኮሚሽነር መንግስቱ ላሎ ተናገሩ፡፡ ይህን ያሉት በባምባሲ ከተማ ከኮሚሽኑ ጋር በጥምረት ከሚሰሩ (የህዝብ ክንፍ) ባለድርሻ አከላት ጋር የኮሚሽኑን ያለፈ አመት አፈፃፀም እና ቀጣይ እቅድ በሚመለከት ውይይት በተደረገበት መድረክ ነው፡፡
በዚሁ መድረክ የተገኙት ክብርት ወ/ሮ አለምነሽ ይባስ (የክልሉ ምክር ቤት ም/አፈጉባኤ እና የሴቶች ፌዴሬሽን ም/ሰብሳቢ) በበኩላቸው ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የሁለም እርብርብ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው የኮሚሽኑ ቅንጅታዊ አሰራር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
የውይይት ዓላማው ኮሚሽኑ ቀደም ብሎ የለያቸው የህዝብ ክንፍ አባላት እና ባለድርሻ አካላት በፀረ-ሙስና ትግሉ ተሳትፏቸው በሚፈለገው ልክ ማሳደግ እና ሚናቸውን በአግባቡ መወጣት እንዲችሉ ማጠናከር መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
በዚህ መድረክ የኮሚሽኑ የተጠናቀቀው የበጀት አመት አፈጻጸም እና የ2015 ዓ.ም ዕቅድ በአቶ አብርሃም ፋሲል (በኮሚሽኑ የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር) ቀርቦ ባለድርሻ አካለት አስተያየት እንዲሰጡበት ተደርጓል፡፡ የዕቅድ መናበቡም በዋነኝነት ከኮሚሽኑ ጋር በትብብር የሚሰሩ አካላት ከኮሚሽኑ ጋር አጣጥመው እንዲያቅዱ እንደሚያስችልም ተመላክቷል፡፡
በተመሳሳይ የባለድርሻ አካላት እና የጥምረቶች የተጠናቀቀው የበጀት አመት አፈጻጸም በአቶ በዛብህ አበጀሁ (በኮሚሽኑ የአውታሮች ኬዝ ቲም አስተባባሪ) ቀርቦ ጠንካራ ጎኖችን ማስቀጠል ድክመቶችን አስተካክሎ የቀጣይ አፈጻፀሙን የተሻለ ለማድረግ የሚያስችል ውይይት ተደርጎበታል፡፡
ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላት አሁን ላይ ያለው ቅንጅታዊ አሰራር ተጠናክሮ መቀጠል ሙስናና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ረገድ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሃሳብ ሰጥተዋል፡፡
በመድረኩ የፍትህ ፎረም አካላት፣ የሐይማኖት ተቋማት የፀረ-ሙስና ንቅናቄ ጥምረት፣ የሴቶች ፌዴሬሽን፣ መምህራን ማህበር፣ ወጣቶች ፌዴሬሽን እና ከኮሚሽኑ ጋር በቅርበት የሚሰሩ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

You, Mengistu Lalo, Yilma Tilahun and 28 others
