የኮሚሽኑ ባለሙያዎች ሙያዊ ድጋፍና እገዛ አደረጉ፤

ወቅታዊ መረጃ

የኮሚሽኑ ባለሙያዎች በመንጌ ወረዳ በመገኘት ለሙስናና ብልሹ አሰራር መተጋገል እንደሚያግዝ የታመነበት ሙያዊ ድጋፍ ለወረዳው አመራሮችና የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች አደረጉ፡፡

ከኮሚሽኑ የሃብት ምዝገባ እና የሙስና መከላከል ዳይሬክተሮች የተወጣጡ የኮሚሽኑ ባለሙዎች በሃብት ማስመዝገብና ማሳወቅ እንዲሁም በሙስናና መከላከል እስትራቴጅዎች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የመንጌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ኢብራሂም መንሱር ድጋፉን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት እገዛው እጅግ ጠቃሚ መሆኑን ገልጸው በተለይ በመጀመሪያው ሩብ አመት መደረጉ ወቅቱን የጠበቀ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

የፀረ-ሙሥና ትግሉ የማህበረሰብ ተሳትፎ እንዲኖረውም ወደታች ወርዶ መሰራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በድጋፉ የመከታተያ ክፍሎች ከኮሚሽኑ ጋር ያላቸውን የሥራ መስተጋብር ማጠናከር እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *