የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን)በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን በማጠናከር የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሠራ እንደሚገኝ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።
በክልሉ በሁሉም ዞኖች፣ ከተማ አሰተዳደሮች እና ወረዳዎች በልማት እና በመልካም አስተዳደር ሥራዎች በክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በድጋፍ እና ክትትል የተከናወኑ ሥራዎች አፈጻጸም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በተገኙበት ተገምግሟል።
ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ በክልሉ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ሊያረጋግጡ የሚችሉ በርካታ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።
በሁሉም ወረዳዎች የተጀመሩ የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ፣ የልማት፣ የፖለቲካ እና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን ይበልጥ ለማጠናከር በትኩረት እየተሠራ ነው ብለዋል።
በክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እስከታች ድረስ በተደረገው የድጋፍና ክትትል የተለዩ ጠንካራ ሥራዎችን በማጠናከር በአፈጻጸም ወቅት በተለዩ ክፍተቶች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራም አቅጣጫዎች መቀመጡን የዘገበው የክልሉ ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ነው፡፡

