ባለፉት አምስት አመታት ከ 93 ሚሊዬን ብር በላይ ከምዝበራ ማዳን መቻሉን ኮሚሽኑ አስታወቀ፡፡

ባለፉት አምስት አመታት ከ 93 ሚሊዬን ብር በላይ ከምዝበራ ማዳን መቻሉን ኮሚሽኑ አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ የአምስት ዓመት (2013-2017 ዓ.ም) እቅድ አፈጻፀሙን ዛሬ በኮሚሽኑ ጽ/ቤት በገመገመበት ወቅት እንዳስታወቀው ተቋሙ በአዋጅ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት ስልታዊ እቅድ ነድፎ ሲንቀሳቀስ መቆየቱ ተወስቷል፡፡ በዚህም መሰረት በሙስናና ብልሹ አሰራር መከላከል በተሰራ ስራ 93, 583, 300 ብር ከምዝበራ በማዳን ለህዝብና ለመንግስት የልማት […]

ተጨማሪ ያነቡ

በመንግሥት ሥራ ላይ ከተሰማሩ ግለሰቦች በሕግ፣ በመርሕ እና በአሠራር የላቀ ሥነ-ምግባር ይጠበቃል..!

በመንግሥት ሥራ ላይ ከተሰማሩ ግለሰቦች በሕግ፣ በመርሕ እና በአሠራር የላቀ ሥነ-ምግባር ይጠበቃል..! የክልሉ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን መልካም ሥነ-ምግባርን በመገንባት ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል የሚያግዝ ስልጠና ለሰራተኞቹ ሰጠ፡፡ የግንዛቤ ማሳደጊያ ስልጠናው የቀረበው በኮሚሽኑ የስልጠና ባለሙያ በአቶ አወቀ ገ/መስቀል ሲሆን በመንግሥት ተቋማት የሥራ ባህል ላይ የሚታዩ ተጨባጭ ሥነ-ምግባራዊ እንከኖች እና የሥራ ሥነ-ምግባር አለማክበር የሚያስከትለው ጉዳት በተመለከተ ሰፊ […]

ተጨማሪ ያነቡ

ኮሚሽኑ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሥራና ክህሎት ቢሮ በስራ እድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዝ ዳይሬክቶሬት ባደረገው የአሰራር ጥናት ላይ ከተቋሙ ባለድርሻዎች ጋር ውይይት አደረገ፡፡

ኮሚሽኑ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሥራና ክህሎት ቢሮ በስራ እድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዝ ዳይሬክቶሬት ባደረገው የአሰራር ጥናት ላይ ከተቋሙ ባለድርሻዎች ጋር ውይይት አደረገ፡፡

ተጨማሪ ያነቡ

ሕግ፣ ደንብና መመሪያን ተፈፃሚ ማድረግ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ቀዳሚ መፍትሔ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታወቀ፡፡

ሕግ፣ ደንብና መመሪያን ተፈፃሚ ማድረግ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ቀዳሚ መፍትሔ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታወቀ፡፡ ህግ፣ ደንብና መመሪያዎችን ከማውጣት ባለፈ ተፈጻሚነታቸውን መከታተል ሙስናና ብልሹ አሰራርን መከላከል የመጀመሪያው መፍትሔ መሆኑን ኮሚሽነር ከማል ሃሰን ገለፁ፡፡ ኮሚሽነሩ ይህን ያሉት በክልሉ ግብርና ቢሮ በግብርና ምርት ግብዓቶች የገጠር ፋይናንስ አቅርቦት የሥራ ዘረፍ ላይ የሙስናና ብልሹ አሰራር ስጋቶችን ለመከላከል በኮሚሽኑ የተካሄደ የአሰራር […]

ተጨማሪ ያነቡ

የፕሮጀክቶችን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ከሙስናና ብልሹ አሰራር የፀዳ አሰራር መዘርጋት ያስፈልጋል – ም/ኮሚሽነር ነጅመዲን አልመሐዲ

የፕሮጀክቶችን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ከሙስናና ብልሹ አሰራር የፀዳ አሰራር መዘርጋት ያስፈልጋል – ም/ኮሚሽነር ነጅመዲን አልመሐዲ በክልሉ የመንገድ ተደራሽነትን በማስፋፋት የማህበረሰብን ኑሮ ማሻሻልና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ታልመው በግብረ ሰናይ ድርጅቶች የሚጠገኑ/የሚሰሩ የመንገድ መሰረተ ልማቶችን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ከሙስናና ብልሹ አሰራር የፀዳ አሰራር መዘርጋት እንደሚያስፈልግ ም/ኮሚሽነር ነጅመዲን አልመሐዲ ገለፁ፡፡ ም/ኮሚሽነሩ አክለውም በቅንጅት መስራት፣ አደረጃጀትን ማጠናከርና ቀጣይነት ያለው የክትትልና የቁጥጥር […]

ተጨማሪ ያነቡ

ኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የምዕራብ ዕዝ 404ኛ ህዳሴ ኮር 3ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በኪነ-ጥበብ ስራዎችና በተለያዩ ዝግጅቶች በአሶሳ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡

የኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የምዕራብ ዕዝ 404ኛ ህዳሴ ኮር 3ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በኪነ-ጥበብ ስራዎችና በተለያዩ ዝግጅቶች በአሶሳ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡ በበዓሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ም/ርዕሰ መስተዳድር የተከበሩ አቶ ጌታሁን አብዲሳን ጨምሮ የዕዙ ከፍተኛ አመራሮችና የክልሉ ባለስልጣናት፣ የክልሉ የፀጥታ አካላት እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች በመታደም ላይ ናቸው፡፡

ተጨማሪ ያነቡ

የሐይማኖት አባቶች የሙስናን አስከፊነት ለምዕመናን በማስተማር ሀገራዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ። ‎

‎ የሐይማኖት አባቶች የሙስናን አስከፊነት ለምዕመናን በማስተማር ሀገራዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ። ‎ ‎ኮሚሽኑ ለሐይማኖት ተቋማት የፀረ-ሙስና ንቅናቄ ጥምረት “በፀረ ሙስና ትግል የሃይማኖት አባቶች ሚና” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ስልጠና ተሰጥቷል። ‎ ‎በስልጠና መድረኩ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ከማል ሀሰን እንዳሉት የሐይማኖት አባቶች በየቤተ-እምነታቸው ትውልዱን በስነ-ምግባር ከማነፅ […]

ተጨማሪ ያነቡ