የሐይማኖት አባቶች የሙስናን አስከፊነት ለምዕመናን በማስተማር ሀገራዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ። ‎

ወቅታዊ መረጃ

የሐይማኖት አባቶች የሙስናን አስከፊነት ለምዕመናን በማስተማር ሀገራዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ።
‎ኮሚሽኑ ለሐይማኖት ተቋማት የፀረ-ሙስና ንቅናቄ ጥምረት “በፀረ ሙስና ትግል የሃይማኖት አባቶች ሚና” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ስልጠና ተሰጥቷል።
‎በስልጠና መድረኩ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ከማል ሀሰን እንዳሉት የሐይማኖት አባቶች በየቤተ-እምነታቸው ትውልዱን በስነ-ምግባር ከማነፅ ባለፈ የሙስናን አስከፊነት ተረድተው ምዕመናኖቻቸውን በማስተማር ሀገራዊ ግዴታቸውን እንዲውጡ ጥሪ አቅርበዋል።
‎ሙስና በሀገር ላይ የሚያስከትለው ሁለንተናዊ ተፅዕኖ እጅግ የከፋ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ ዜጎች በየተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ከሙስና በፀዳ መልኩ ማግኜት ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
‎ሙስናን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ሁሉም ባለድረሻ አካላት የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርምም ኮሚሽነሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
‎የኮሚሽኑ የሙስና ወንጀሎችና ብልሹ አሰራር መከላከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጊሳ ዚፋህ በበኩላቸው የሐይማኖት አባቶች የሙስናን አፀያፊነትና የሚያስከትለውን ውስበስብ ተፅዕኖ ተረድተው እንዲሰሩ ጠይቀዋል፡፡
‎ኮሚሽኑ በስነ-ምግባር ጉድለት ምክንያት ሙስና የሚፈፀሙ አካላትን ቀድሞ የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባር እያከናወነ ይገኛልም ብለዋል፡፡
‎በፀረ-ሙስና ትግል የሐይማኖት አባቶች ሚና” በሚለው ርዕሰ ጉዳይ በተዘጋጀው ስልጠና የተሳተፉ የሐይማኖት አባቶች እንዳሉት ሙስና መስጠትም ሆነ መቀበል በሐይማኖታዊ አስተምህሮ ውስጥ ኃጢያት መሆኑን ጠቅሰዋል።
# BGM

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *