(አሶሳ፣ ታህሳስ 04/2015 ዓ.ም) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት 7 አባላት ያሉት የጸረ-ሙስና ኮሚቴ አቋቋመ።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ትግል በተደራጀ መልኩ ውጤታማ ለማድረግ 7 አባላት ያሉት የጸረ-ሙስና ኮሚቴ መቋቋሙን አስታውቀዋል።
የክልሉ መንግስት ሙስናና ብልሹ አሠራርን በመከላከል ህብረተሠቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎችን ለማጠናከር በቁርጠኝነት ይሠራል ያሉት አቶ አሻድሊ፣ የጸረ-ሙስና ትግሉ የሁሉንም የተቀናጀ ተሳትፎ እንደሚፈልግም ገልጸዋል።
በክልሉ የተቋቋመው የጸረ-ሙስና ኮሚቴ ከዛሬ ጀምሮ ወደሥራ እንደሚገባ ጠቁመው፣ ለውጤታማነቱም የክልሉ ሕዝብ ጥቆማ ከመስጠት ጀምሮ አስፈላጊውን ድጋፍ እዲያደርግ አቶ አሻድሊ ጥሪ አቅርበዋል።
የክልሉ የጸረ-ሙስና ኮሚቴ አባላትም፦
1ኛ. አቶ ሠይድ ባበክር፦ የኮሚቴው ሠብሳቢ
2ኛ. ኮሚሽነር መንግስቱ ላሎ፦ አባል
3ኛ. ምክትል ኮሚሽነር አምሳሉ ኢረና፦ አባል
4ኛ. አቶ ነጂ ኖኖ፦ አባል
5ኛ. አቶ ከማል ሀሰን፦ አባል
6ኛ. አቶ መሀመድ ሃሚድ፦ አባል
7ኛ. አቶ ሙክታር አብዱላሂ፦ አባል ሆነው ተሰይመዋል።

የቤጉክ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን and 2 others
