ምልከታው ኮሚሽኑ ያሉትን ጠንካራ ጎኖች ለማስቀጠልና ክፍተቶችን በመዝጋት የተሻለ የፀረ-ሙስና ትግልና የሥነ-ምግባር ግንባታ ለማካሄድ ያግዘናል – ኮሚሽነር ከማል ሃሰን

ወቅታዊ መረጃ

2ኛው አገር ዓቀፍ የኮሚሽኖች የአቻ ለአቻ ድጋፋዊ ምልከታ (ሱፐርቪዥን)  በሁሉም የክልል እና ከተማ አስተዳደር የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች የድጋፍ፣ የክትትልና የግረብረ መልስ ስራዎች እየተሰራ ሲሆን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሥነ-ምግባና ፀረ-ሙስና ኮሚሽንም ምልከታው እየተካሄደ ነው፡፡

 

ምልከታው ኮሚሽኑ ያሉትን ጠንካራ ጎኖች ለማስቀጠልና ክፍተቶችን በመዝጋት የተሻለ የፀረ-ሙስና ትግልና የሥነ-ምግባር ግንባታ ለማካሄድ  ያግዘናል ያሉት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ከማል ሃሰን፤  መሰል ምልከታዎች ለተቋሙ አፈፃፀም አወንታዊ ሚና እንዳለቸው ከፌደራል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለምልከታ ከመጣው ቡድን ጋር ባደረጉት ውይይት  ተናግረዋል፡፡

 

ድጋፋዊ ምልከታው በዋናነት በ2017 በጀት ዓመት ኮሚሽኑ ያከናወናቸውን የሙስና መከላከልና የሥነ-ምግባር ግንባታ ስራዎች የሚያካትት ነው፡፡

 

በተጨማሪም በባለፈው በጀት አመት በኮሚሽኑ የተሰሩ መልካም ተሞክሮዎችን በመለየት ለሌሎች አቻ ኮሚሽኖች ልምድ የሚቀመርበት  መሆኑን   የምልከታ ቡድኑ በተለይም ስለ ምልከታው መመዘኛ ቅፅ (ቼክ ሊስት) ማብራሪያና ምላሽ በሰጡበት ወቅት  ለኮሚሽኑ አመራሮችና የሥራ ኃላፊዎች አስታውቋል፡፡

 

የፌደራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን 2ተኛውን ዙር አገር ዓቀፍ የኮሚሽኖች የአቻ ለአቻ ድጋፋዊ ምልከታ (ሱፐርቪዥን) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ   ክልልን ጨምሮ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በማካሄድ ላይ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *