ከ128, ዐዐዐ በላይ ለሚሆኑ አካላት ስራቸውን በተሻለ ሥነ-ምግባር መስራት የሚያስችል ስልጠና መስጠት መቻሉን ኮሚሽኑ አስታወቀ፡፡
****************
(አሶሳ፣ ግንቦት 23/2ዐ15፤ ቤጉ-ፀረ-ሙስና) የቤኒቫንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን 128,076 ለሚሆኑ የህ/ሰብ ክፍሎች የሥነ-ምግባር ስልጠናዎች መስጠት መቻሉን ኮሚሽነር መንግስቱ ላሎ ገልፀዋል፡፡
በስልጠናው ሙያዊ ሥነ-ምግባር፣ የሞራል እሴቶች እና ሥነ-ምግባራዊ አመራር ከተሰጡት የሥልጠና ርዕሶች ጥቂቶቹ መሆናቸው በያዝነው የበጀት አመት የዘጠኝ ወር አፈፃፀም በተገመገመበት ወቅት ኃላፊው አክለው ጠቁመዋል፡፡
በስልጠናውም የመንግስት ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች፣ ሠራተኞች፣ የፍትህ አካላት እና የመከታተያ ክፍሎች የተሰጣቸውን ኃላፊነት በተሻለ ስነ-ምግባር መምራት የሚያስችላቸውን ስልጠና መውሰድ መቻላቸው ተመላክቷል፡፡
ተቋሙ በትውልድ የሥነ-ምግባር ግንባታ ላይ ትኩረት በማድረግ በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡

