በ UIIDP የገንዘብ ድጋፍ በአሶሳ ከተማ የተሰሩ የመሰረተ-ልማቶች አፈፃጸም ግምገማ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
በ UIIDP የገንዘብ ድጋፍ በአሶሳ ከተማ የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ የመሰረተ-ልማቶች ያሉበት ደረጃ ከፌደራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በተወጣጡ ሰባት አባላትን ባካተተ የጥናት ቡድን የማረጋገጥ ሥራ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
የጥናት ቡድኑ ትኩረት ካደረገባቸው ጉዳዮች መካከል፤ በፕሮጀክቶች አፈፃፀም ወቅት ፤ሙስናን መከላከል የሚያስችሉ የአሰራር ስርዓት መኖር፤ የአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች አደረጃጀት ግልጸኝነት፤ የጥቅም ግጭት የማስቀረት አሰራር መኖር፤ የግንባታ ስራ ጥራት ቁጥጥር እና የሕዝብ የጥቆማ መስጫ ስርዓት መኖር ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
ቡድኑ ከክልሉ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን፣ ከክልሉ የከተማ ልማትና ከአሶሳ ከተማ አስተዳደር አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ውይይቶችን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
ጥናቱን ማካሄድ ያስፈለገበት አላማ UIIDP የሚያደርገው የገንዘብ ድጋፍ በትክክል ለታለመለት ዓላማ ብቻ ሥራ ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ ሲሆን ይህም ለቀጣይ የልማት ሥራዎች አፈፃጸም መልካም ዕድልን ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የጥናት ቡድኑ አባላት በክልሉ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን፣ በክልሉ የከተማ ልማት ቢሮ እና በአሶሳ ከተማ አስተዳደር አመራሮችና ባለሙያዎች እየተደረገላቸው ላለው ከፍተኛ ትብብር ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡





