ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ከክልሉ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በቅርበት እንደሚሰራ የማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ አስታወቀ፡፡

ወቅታዊ መረጃ

ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል በሚደረግ ዘርፈ ብዙ መተጋገል ከኮሚሽኑ ጋር በቅርበት መስራት እንደሚፈልጉ የማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ ም/አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ሐብቴ ገልፀዋል፡፡

 

ም/አስተዳዳሪው አክለውም ሙስናና ብልሹ አሰራር ለመከላከል ልዩ ወረዳው  በሚያደረገው ጥረት ኮሚሽኑ ቀጣይነት ያለው  የሙስና መከላከል ስራ   (የሥልጠና፣ የሐብት ምዝገባ፣   የድጋፍና የክትትል ስራዎችን) በመስራት  እንዲያግዛቸው ጠይቀዋል፡፡

 

ኮሚሽኑ በማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ የሙስና መከላከል ስራዎች እየተሰሩ ያሉበትን ሁኔታ በሚመለከት የድጋፍና ክትትል ስራ በመስራት ላይ ነው፡፡ በቀጣይም የክትትልና የድጋፍ ቡድኑ በለያቸው ክፍተቶች መነሻነት  የስራ ሥነ-ምግባርና

የሙስና መከላከል ይዘቶች ላይ  በወረዳው ለሚሰሩ አመራሮችና ሰራተኞች ስልጠና የሚሰጥ ይሆናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *