የስራ ስነ-ምግባር መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና ዘርፈ ብዙ ዉጤታማነትን ለማሳደግ የጎላ ሚና አለው – አቶ ገዛኸኝ የኔው
(ቶንጎ ፣ ታህሳስ 10/2017 ዓ.ም) ኮሚሽኑ በማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ ለሚሰሩ አመራሮችና የመንግስት ሰራተኞች የሥራ ሥነ-ምግባርን በሚመለከት የግንዛቤ ሥልጠና ሰጠ፡፡
ስልጠናውን የሰጡት በኮሚሽኑ የትምህርትና ስልጠና ቡድን መሪ አቶ ገዛኸኝ የኔው የሥራ ስነ-ምግባር መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ውጤታማነትን ለማሳደግ አይነተኛ ሚና እንደሚጫወት ባቀረቡት ሰነድ አስረድተዋል፡፡
በመድረኩ የተገኙት የማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ ም/ አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ሀብቴ በበኩላቸው ስልጠናው የመንግስት ኃላፊነትንና ስራን በአግባቡ ለመመራት እንደሚያግዝ ገልፀው፤ የወረዳው አመራሮችና ሰራተኞች ከሙስናና ብልሹ አሰራር የፀዳ አገልግሎት በመስጠት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት እንዲያረጋጋጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡





All reactions:
You, Mengistu Lalo, የቤጉክ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን and 2 others
