ኮሚሽኑ በካማሽ ዞን ስር ለሚገኙት የሰዳልና ደምቤ ወረዳ አመራሮችና የማኔጅመንት አካላት ስልጠና ሰጠ፡፡

ወቅታዊ መረጃ

ኮሚሽኑ በካማሽ ዞን ስር ለሚገኙት የሰዳልና ገምቤ ወረዳ የተቋማት አመራሮችና የማኔጅመንት አካላት በፀረ-ሙስና ትግሉ የአመራሩ ሚና በሚል ርዕስ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

 

ስልጠናውን የሰጡት በኮሚሽኑ የፊት ለፊት የሥነ-ምግባር ትምህርትና ስልጠና ባለሙ አቶ አወቀ ገ/መስቀል ከግዥና  ፋይናንስ፣ ከሰራተኛ ቅጥርና ጥቅማጥቅም፣ በማዕድን ዘርፍና  ተጓዳኝ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ ስለሚስተዋል  ሙስናና ብልሹ አሰራርና  መወሰድ ስለሚገባው መፍትሔ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

 

በሌላ ዜና  ከላይ በተጠቀሱት ወረዳዎች በተቋማት ተመድበው ለሚሰሩ የመከታተያ ክፍል ባለሙያዎች በአሰቸኳይ የሙስና መከላከልና የሐብት ማስመዝገብና ማሳወቅ ስራዎችን በሚመለከት በኮሚሽኑ ባለሙያዎች የክትትልና ድጋፍ ስራዎች በመሰራት ላይ ናቸው፡፡

 

መሰል ስልጠናዎች ተከታታይነት እንዲኖራቸውና በሙስናና ብልሹ አሰራር በሚሳተፉ አካላት ላይም ኮሚሽኑ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመቀናጀት የህግ የበላይነት እንዲከበር አበክሮ እንዲሰራ የስልጠናው ተሳታፊዎች ጠይቀዋል፡፡

 

ኮሚሽኑ በካማሽ ዞን የሚያደርገው የሥልጠና፣  ድጋፍና ክትትል ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፤ በዞኑ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል በሚደረገው መተጋገል ከፍተኛ መነቃቃትን እንደሚፈጥር ይጠበቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *