የኮሚሽኑ የሥልጠና፣ የድጋፍናክትትል ቡድን በካማሺ ዞን በዛይ እና ምዥጋ ወረዳዎች በመንቀሳቀስ ለየሴክተር መ/ቤት ማኔጅመንት አካላት፣ ለሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያዎችና የሥነ-ምግባር ፀረሙስና ፎካል ፐርሰኖች በሥራ ሥነ-ምግባር፣ በመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሠጣጥና በሙስናና ብልሹ አሰራር ይበልጥ ተጋላጭ በሆኑ የሥራ ዘርፎች ማለትም በፋይናንስ አጠቃቀም፣ በግዥና ንብረት አስተዳደር እንዲሁም በማዕድን ዘርፎች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማሳደጊያ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል።
የድጋፍና ክትትል ቡድኑ በዞኑ የሐብት ምዝገባና ሌሎች የሙስና መከላከል ሥራዎች ያሉበትን ሁኔታ በመመልከት ሠፊ የድጋፍ ሥራዎችን ለመከታተያ ክፍል ባለሙያዎች ያደረገ ሲሆን ተመሣሣይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች ለዞን፣ ለከተማ አስተዳደር፣ ለካማሺ ቴ/ሙ/ኮሌጅና ለካማሺ ሆስፒታል አመራሮችና ሰራተኞች የሚሠጥ ይሆናል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች የተሰጡ ሥልጠናዎች እና የተደረጉ ድጋፎች በቀጣይ ሥራዎቻቸውን ሲያከናውኑ ከሙስናና ብልሹ አሰራር በፀዳ መልኩ ለማከናወን መነሳሳትና አቅም እንደፈጠረላቸው ገልፀዋል።

