የክልል እና ከተማ አስተዳደር የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች፣ የሙስና መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነሮች እና የሥራ ኃላፊዎች በ2017 ግማሽ የበጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ላይ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው አገር አቀፍ የምክክር መድረክ ተጠናቋል።
በምክክር መድረኩ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት አገራዊ የሙስና መከላከል ጥናት፣ የአስቸኳይ ሙስና መከላከል፣ የሙስና መረጃ አስተዳደር እና የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ እንዲሁም የሀብት ምንጭ ትክክለኛነት የማረጋገጥ ሥራ አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች እንዳሉት ከጥናትና ከዜጎች የሚቀርቡ የሙስና መረጃዎች ወቅታዊ ምላሽ ማግኘት እንዳለባቸው ገልፀዋል።
በምክክር መድረኩ ከላይ በስድስት ወር የቀረቡ አፈፃፀሞች ወጥነት እንዲኖራቸውና በግልፅ የአሰራር ማንዋል መከናወን እንዳለባቸው የጋራ ግንዛቤ ተፈጥሯል።
በተመሳሳይ በዚህ መድረክ የልምድ ልውውጥ የተደረገበት፣ አገራዊ መረጃ የተገኘበት እና በቀጣይ ሥራዎች ላይ የጋራ መግባባትና አቅጣጫ መያዝ የተቻለበት መሆኑ ተመለክቷል፡፡
በምክክር መድረኩ በተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይም በቀጣይ በሚካሄደው አገር አቀፍ የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች ትስስር ጉባዔ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል።

