
አምሰት ሚሊዮን ዜጎች የዲጂታል ቴክኖሎጂ ስልጠና ተጠቃሚ የሚሆኑበት የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቪ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ይፋ መሆኑን ተከትሎ ዜጎች ተገቢው የዲጂታል ክህሎት እንዲኖራቸው በማድረግ ስራ እና ሀብትን በመፍጠር የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን ለማቀጣጠል የሚረዳ ፕሮግራም መሆኑ መገለፁ ይታወሳል፡፡
ይህን ሃገራዊ ኢንሼቲቭ ለማሳካትም እንደ ክልል የተሰጠውን እድል የኮሚሽኑ አመራሮችና ባለሙያዎች በመጠቀም እራሳቸውን ለዲጅታል ኢኮኖሚው ዝግጁ እንዲያደርጉ ኮሚሽነር ከማል ሀሰን ጥሪ አድርገዋል፡፡
