የኮሚሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች 13350 ብር የሚገመት የትምህርት ቁሳቁስ፤ ድጋፍ ለሚሹ 13 ተማሪዎች ለግሰዋል፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ነጅመዲን አልመሃዲ ድጋፉን ባበረከቱበት ወቅት እንዳሉት ተማሪዎች በስነ-ምግባራቸው የተመሰገኑ፣ በትምህርታቸው ጠንካራ መሆን እንደሚገባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ይህን ሰናይ ተግባርም ተቋሙ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡
የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች 13 ተማሪዎችን በየአመቱ በቋሚነት እንደሚደግፉ የሚታወቅ ነው፡፡

