ኮሚሽኑ የክረምት የበጎ አድራጎት ስራን ምክንያት በማድረግ ድጋፍ ለሚሹ 100 የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በጉባ ወረዳ ማንኩሽ ከተማ አድርጓል፡፡
የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ የተደረገላት ተማሪ ሰሎሜ ሙሳ (የማንኩሽ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ ) ድጋፉ ያለምንም ሃሳብ ትምህርቷን መማር እንደሚያስችላት ገልፃ፤ በተደረገላት ድጋፍ ደስተኛ መሆኗን ተናግራለች፡፡
በተመሳሳይ ተማሪ ማህሌት አዳነ (የማንኩሽ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ ) ድገፉ በትምህርቷ ጠንካራ እንደሚያደርጋት ገልጻ፤ እገዛው ነገ ላይ እሷም ለሌሎች መድረስ እንዳለባት የተማረችበት መሆኑን ጠቁማለች፡፡
በድጋፍ አሰጣጥ መርሃ ግብር መልዕክት ያስተላለፉት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሐብት ማስመዝገብና ማሳወቅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኤሊያስ ወዲሻ ድጋፉ ማህበረሰቡ መተጋገዝና መረዳዳትን አጠናክሮ ለማስቀጠልና በጎነትን ለትውልድ ማውረስን ዓላማው ያደረገ መሆኑን ገልፀው፡፡ ማህበረሰቡ መደጋገፍን ችግሮችን ለማለፍ እንደ አንድ መሳሪያ ሊጠቀም እነደሚገባ ነው የተናገሩት፡፡
የጉባ ወረዳ ም/ዋና አስተዳዳሪ አቶ በኬ ድርዱም በበኩላች ድገፉ በዚህ መልኩ እስከታች መውረዱን አድንቀው ምስጋና አቅርበዋል፤ መሰል ድጋፎች ተጠናክረው መቀጠልም የማህበረሰቡን አብሮነት የሚያጠናክሩ መተጋገዝና መረዳዳት ያለውን መልካም ጎን የሚያሳይ መሆኑን አፅኖት ሰጥተው፤ የወረዳውን ነዋሪ ተጠቃሚ የሚያደርጉ መሰል የድጋፍና የበጎ አድራጎት ስራዎች በወረዳ ደረጃም እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
ድጋፉን የወረዳው ምክትል ዋና አስተዳደሪ አቶ በኬ ድርዱም ጨምሮ የኮሚሽኑ የሐብት ማስመዝገብና ማሳወቅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኤሊያስ ወዲሻ እና በወረዳው በየደጃው የሚገኙ አመራሮች ለተማሪዎች አበርክተዋል፡፡

