በአሶሳ ከተማ ለሚገኙ የንግድ እና የመኖሪያ ቤቶች የአከራይ ተከራይ የህግ ረቂቅ ለማውጣት እየሰራ መሆኑን የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አስታወቀ *************

ወቅታዊ መረጃ

በአሶሳ ከተማ ለሚገኙ የንግድ እና የመኖሪያ ቤቶች የአከራይ ተከራይ የህግ ረቂቅ ለማውጣት እየሰራ መሆኑን የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አስታወቀ።

 

ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚዲያ ጋር ቆይታ ያደረጉት

 

በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ም/ቤት የህግ እና አስተዳድር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ተክለአብ አባይ በከተማዋ የሚታየውን የንግድ እና መኖሪያ ቤቶች የኪራይ ዋጋ መናርን ለመግታት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።

 

በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች እየተተገበረ ያለውን የአከራይ እና ተከራይ ህግ በአሶሳ ከተማም ለመተግበር ከሌሎች ከተሞች የልምድ ልውውጥ ሲደረግ መቆየቱን አቶ ተክለአብ አንስተዋል።

የተቀመረዉን ልምድ ተግባራዊ ለማድረግም የህግ ረቂቅ በማውጣት በተያዘው ዓመት ወደ ስራ እንደሚገባ ተናግረዋል።

 

የአከራይ እና ተከራይ ህግ መውጣቱ ህጋዊና ፍትሀዊ የሆነ የግብር አጣጣል እንዲኖር የሚያግዝ እና በህብረተሰቡ ዘንድ የሚነሱ ቅሬታዎችን በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀርፍ መሆኑን አመላክተዋል።

 

 

ረቂቅ ህጉ ወጥቶ ተግባራዊ እስኪደረግ ድረስም ክትትል እና ቁጥጥር የሚያደርግ ግብረ ሀይል መቋቋሙን እና የማረጋጋት ስራ የሚሰራ መሆኑን ማስታወቃቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚዲያ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *