በተቋማዊ እና ብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ የማይደራደሩ ታማኝ አገልጋዮች ያስፈልጉናል፡- ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር)

ወቅታዊ መረጃ

በተቋማዊ እና ብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ የማይደራደሩ ታማኝ አገልጋዮች፣ የሥራ ኃላፊዎች፣ ሠራተኞች እና የተቋማት ተገልጋዮች ያስፈልጉናል ሲሉ የፊዴራል የሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) ተናገሩ።

 

22ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን ማጠቃለያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

 

ከለውጡ ወዲህ የፀረ-ሙስና ትግል ጉድለትን የሚያርሙ ሥራዎች መሠራታቸውን እና ሕጎችን ማሻሻል እና የፀረ ሙስና ትግል ትብብር እንዲያድግ መደረጉን የፊዴራል የሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) በመድረኩ ገልጸዋል።

 

በተሻሻለው የሀብት ማሳወቂያ እና ማስመዝገቢያ አዋጅ መሠረት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ የመንግሥት ተቋማት መሪዎች ሃብታቸውን ማሳወቃቸውንም ጠቅሰዋል።

 

ኮሚሽነሩ ተቋም እና ዘርፍ ተኮር ሥራዎችን ማጠናከር፣ የፍትሕ እና የዳኝነት አካላትን አቅም መገንባት ላይ ትኩረት መደረጉን በማንሣትም ከለውጡ ዓመታት በፊት በሥነ-ምግባር ጉድለት አደጋ ተጋርጦባቸው የነበሩ የልማት ፕሮጀክቶችን የመታደግ ሥራም ተሠርቷል ብለዋል።

 

አስተዳደራዊ እና ቢሮክራሲያዊ ሙስና ቀጣይ የቤት ሥራችን ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፣ ምንጩ ያልታወቀ ሀብት እንዳይፈጠር ኮሚሽኑ ተገቢውን ክትትል ያደርጋል ነው ያሉት።

 

የፌዴራል መንግሥት ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች በዲጂታል የሀብት ምዝገባ አሠራር መሠረት ሀብታቸውን የማሳወቅ እና የማስመዝገብ ንቅናቄ መፈጠሩንም ጠቁመዋል።

የተቋማት ሠራተኞች እና አመራሮች ራሳቸውን ከሙስና ፅዱ በማድረግ፣ ተቋሞቻቸው ለሙሰኞች እንዳይጋለጡ ለመከላከል ሕጋዊ እና ሞራላዊ ግዴታቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።

 

#የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *