ኮሚሽኑ ቀሪ የስድት ወር ስራዎችን በውጤታማነት መፈፀም በሚያስችለው የስራ መዘርዝር ላይ ውይይት አደረገ፡፡

ወቅታዊ መረጃ

 

ኮሚሽኑ ቀሪ የስድት ወር ስራዎችን በውጤታማነት መፈፀም በሚያስችለው የስራ መዘርዝር ላይ ውይይት አደረገ፡፡

 

የኮሚሽኑ ቀሪ የስድስት ወር ስራዎች ዝርዝር ለኮሚሽኑ የበላይ አመራሮችና የሥራ ኃላፊዎች ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡

 

በውይይቱ ምክትል ኮሚሽነር ነጅመዲን አልመሐዲ ቀሪ ስራዎች በዚህ ደረጃ መቅረባቸው የሚበረታታና ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው ብለዋል፡፡

 

ተግባራቱን ለመፈፀምና የተቋሙን የዕቅድ አፈጻፀም ውጤታማነት ለማሳደግም ከወዲሁ በትኩረተ እንደሚሰራና   ስራዎችን ለመስራት የሚያስችል አስቻይ ሁኔታ  ለመፍጠር ጥረት እንደሚደረግ ጨምረው  ተናግረዋል፡፡

 

የኮሚሽኑ የእቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር አቶ አብርሐም ፋሲል በበኩላቸው የኮሚሽኑ አፈፃፀም የሁሉም የሥራ ክፍል ድምር ውጤት መሆኑን ገልፀው፤ ቀሪ የስድስት ወር ዝርዝር ስራዎችን በአሰራር ጥናት፣ በስነ-ምግባርና ስልጠና፣ በአውታሮች አደረጃጀት፣ በሐብት ምዝገባና ማሳወቅ እንዲሁም በኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ሸንሽነው አቅርበዋል፡፡

 

አቶ አብርሐም ፋሲል  በተለይም የኮሚሽኑ ዓላማ ፈፃሚ ዳይሬክተሮች ለዕቅዳቸው ውጤታማነት እንዲተጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *