የፍትህ አካላትን ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር የተቋማቱን ውጤታማነት እንደሚያሳድግ ተመላከተ፡፡    

ወቅታዊ መረጃ

 

በአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት  መሃመድ   ማህሙድ  የተመራ የክልሉ ፍትህ ፎረም አባላት በኩርሙክ ወረዳ ተገኝተው  የፍትህ አካላት  ቅንጅታዊ አሰራርን  ውጤታማነት በሚያጎለብቱ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

 

በውይይቱ ወረዳው ጠረፋማና ከማዕድን ሀብት ጋር ተያያዞ  ከፍተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚያስተናግድ ከመሆኑ አንጻር  አልፎ አልፎ የሚፈጠሩ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የፍትህ አካሉ ድርብ ኃላፊነት እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡  ይህንን በመገንዘብ በትጋት መስራት እንደሚገባ አፅንኦት የሰጡት  የክልሉን ፍትህ ፎረም አካላት የመሩት የአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት መሃመድ ማህሙድ ናቸው፡፡

 

የኩርሙክ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከማል መሐመድ በበኩላቸው የክልሉ የፍትህ ተቋማት ፎረም የድጋፍና የክትትል ስራ የተቋማቱን ስራ የሚያጎለበት በመሆኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 

በተያያዘ ዜና  በወረዳው አምስት ቀበሌዎች የባህል ፍርድ ቤት ለማቋቋም በዕቅድ መያዙን  መነሻ በማድረግ  በወረዳው  የባህል ፍርድ ቤቶችን የሚከተታተልና የሚቆጣጠር የባህል ፍርድ ቤት ምክር ቤት እንዲቋቋም አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡

 

የባህል ፍርድ ቤቶች መደበኛ ፍርድ ቤቶች ላይ የሚያጋጥመውን የሥራ ጫና በማቃለል፤   ባለጉዳዮች ጊዜ፣ ጉልበታቸውንና ገንዘባቸውን ቆጥበው ጉዳያቸውን እንዲፈፅሙ በማድረግና የተገልጋዮችን እንግልት በመቀነስ ረገድ አወንታዊ ሚና እንዳለው ይታመናል፡፡

 

 

በተጨማሪም የክልሉ የፍትህ ፎረም አካለት  የኩርሙክ ወረዳ ፍርድ ቤት፣ ፍትህ ጽ/ቤት እና የፖሊስ ጽ/ቤት የኤግዚቪትና የተጠርጣሪዎች አያያዝ ሁኔታ በአካል በመገኘት ተመልክተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *