22ኛውን አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በዓል መነሻ በማድረግ በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ውይይት ተደረገ፡፡

ወቅታዊ መረጃ

 

 

 

በሰነዱ በመንግስት መስሪያ ቤቶች እና የልማት ድርጅቶች የሚስተዋሉ፤ የተለያዩ የሙስና ዓይነቶች መዳሰሳቸውን ያወሱት የኮሚሽኑ የሙስና ወንጀሎችና ብልሹ አሰራር መከላከል ዳይሬክተር አቶ ጊሳ ዚፍሃ በተዋረድ የሚገኙ የመንግስት ተቋማት በሰነዱ ላይ በተነሱ ጉዳዮች ላይ  የሰላ ውይይት ማድረግ፣ የሙስና ወንጀል ተጋላጭነት ባለባቸዉ የዉስጥ አሰራሮች  ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ መያዝ፣ ችግሩን ለመፍታትም ጠንካራና ዘመኑን የዋጀ የፀረ-ሙስና ትግል ማድረግ እንደሚገባ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

 

አሰራሮችን በቴክኖሎጅ ማገዝና ማዘመን ሙስናና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ረገድ  አይነተኛ ሚና አለው፡፡ ዜጎች ቀልጣፋና ግልጽነት ያለው፣ ከሰው እጅ ንክኪ ነጻ አገልግሎት ማግኘት  የሚችሉት አገልግሎት አሰጣጡ በቴክኖሎጂ ሲታገዝና ሲዘመን ነው፡፡ ይህም ሙስናና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ረገድ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ይታመናል፡፡

 

ኮሚሽኑ ከሰሞኑ 22ኛውን አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “ትውልድን በሥነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሰራር! በሚል መሪ ቃል ለማክበር ባዘጋጀው ረቂቅ ሰነድ ላይ እንደተገለፀው፤ አንዳንድ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልግሎትን በዘመነ አኳኋን ተደራሽ ለማድረግ እየሄዱበት ያለው እርቀት አድናቆት ያሻዋል፡፡

 

የተዘረጉ  የዲጂታል ቴክኖሎጂ አሠራሮችም  አስተማማኝ የደህንነት ጥበቃ የሚደረግላቸው እና ለተገልጋዮች   ምቹ እንዲሆኑ አበክሮ መስራት እንደሚገባም ሰነዱን ያቀረቡት የኮሚሽኑ የፊት ለፊት የሥነ-ምግባር ትምህርትና ስልጠና ባለሙያ አቶ አወቀ ገ/መስቀል አስረድተዋል፡፡

 

በፌደራል፤ በክልልና በከተማ አስተዳደር ኮሚሽኖች በተካሄዱ  ተከታታይ ጥናቶችና የመረጃ ማመንጨት ተግባራት ደረጃው ቢለያይም በተለያዩ   ዘርፎች እና ተቋማት ለሙስና ተጋላጭ የሆኑ የዉስጥ አሰራር ሥርዓት መኖራቸዉ ተረጋግጧል፡፡

 

ለዚህም በአሉታዊ ጎኑ አስቻይ ሁኔታ የሚፈጥረዉ፤ የተቋማት የዉስጥ አሰራር  አለመዘመን መሆኑ በሰነዱ በግልፅ ተቀምጧል፡፡

 

 

ሙስናና ብልሹ አሰራን በመከላከል ረገድ የአመራሩ ቁርጠኝነት  ዜጎች የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኙ እንደሚያደርግ በሰነዱ ሲገለፅ ከችግሩ ገዝፈዉ የላቀ እና የተቀናጀ የፀረ-ሙስና ትግል የሚያካሂዱ  አመራሮች በአጭር ጊዜ  ተቋማቸውን  ከሙስና ተጋላጭነት እያነጹ እንደሚገኙ በማሳያነት ተወስቷል፡፡

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *