የሰነድ ማረጋገጫንና የምዝገባ አገልግሎትን ዲጂታላይዝድ በማድረግ ተገልጋዩን ከእንግልት ለማስቀረት እየተሰራ ነው

ወቅታዊ መረጃ
የሰነድ ማረጋገጫንና የምዝገባ አገልግሎትን ዲጂታላይዝድ በማድረግ ተገልጋዩን ከእንግልት ለማስቀረት እየተሰራ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዋና አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አስካለች አልቦሮ አስታወቁ።
የክልሉ ፍትህ ቢሮ DARS ቴክኖሎጂ የኦንላይን አገልግሎትን በይፋ አስጀምሯል።
‎በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዋና አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አስካለች አልቦሮ እንዳሉት በክልሉ ሲሰጥ የቆየው የሰነድ ማረጋገጥ አገልግሎት ደህንነቱን ባልጠበቀ መልኩ ሲስራ መቆየቱን አስታውሰዋል።
‎ ሆኖም የሰነድ ማረጋገጥና የምዝገባ አገልግሎት ዘመኑን በዋጀ ዲጂታላይዝ በማድረግ ተገልጋዩን ከእንግልት ለማስቀረት እየተሰራ ስለመሆኑን ወይዘሮ አስካል ተናግረዋል።
‎ለስኬታማነቱም የባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና እንዲሁም ግብዓት በማሟላት የክትትልና ድጋፍ ስራዎች መስራታቸውንም አፈ ጉባኤዋ ጠቁመዋል።
‎የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ መሃመድ ሀሚድ በሰነድ ማረጋገጥና ምዝገባ አገልግሎት ላይ የሚስተዋለውን እንግልትና የአሰራር ችግር ለመቅረፍ DARS ቴክኖሎጂ የኦንላይን አገልግሎትን በይፋ መጀመሩን ተናግረዋል።
‎የኢፌዴሪ ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀሚድ ኪኒሶ ቀልጣፋ፣ ተዓማኒነቱና ድህነቱ የተረጋገጠ ዲጂታል ኢትዮጵያን ለመገንባት ቴክኖሎጂው አይነተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል።
‎የሀገሪቱ የመረጃ ስርዓት በአንድ ማዕከል መሆኑ ደግሞ ለተለያዩ አገልግሎቶች መሳለጥ ሚናው የጎላ ነው ብለዋል አቶ ሀሚድ።
‎ተደራሽነቱ ላይም በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ አስገንዝበዋል።
‎የተቋሙ ሰራተኞች እና የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች በበኩላቸው ቴክኖሎጂው ሀሰተኛ መረጃን ከማስቀረት ባሻገር ቀልጣፋ፣ ምቹ ጊዜና ጉልበት ቆጣቢ በመሆኑ በሌሎች ተቋማትም መተግበር እንዳለበት ተናግረዋል።
‎የሰነድ ማረጋገጥና ምዝገባ ኦንላይን አገልግሎት ማስጀመሪያ ላይ ድጋፍ ላደረጉ ተቋማት ምስጋናና ሰርተፊኬት መስጠቱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚዲያ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *