ት/ቤቶች በመልካም ሥነ-ምግባር የታነፀ ትውልድ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የሚጠበቅባቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

ወቅታዊ መረጃ
(ቶንጎ፣ ታህሳስ 11/2017 ዓ.ም) ት/ቤቶች በሥነ-ምግባ የታነፀ እና በዕውቀት የተካነ ማህበረሰብ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ሚና እየተወጡ እንደሆነ የማኦ ኮሞ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ም/ርዕሰ መምህር እስራኤል መልካ ገለፁ፡፡
ለዚህም በት/ቤቱ በስራ ላይ የሚገኘውን የግብረ-ገብና የፀረ-ሙስና ክብብ የተማሪዎችን ባህሪ ለማስተካከልና እና ውጤታውን ለማሻሻል እየተጠቀሙበት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
በተመሳሳይ በቶንጐ ከተማ የሚገኘው የአባ ሃሩን አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ም/ርዕሰ መምህርት አስናቀች ወዳጄ ክበቡ የተፈለገወን ውጤት እንዲያስመዘገብ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እንዲሰጧቸው እና የድጋፍና ክትትል ስራዎች እንዲሰሩላቸው ጠይቀዋል፡፡
ኮሚሽኑ ከክልሉ ት/ቢሮ ጋር በመተባበር በማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ በሚገኝ ት/ቤቶች የተማሪዎች የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ክበብ አደረጃጀትና የሥራ እንቅስቃሴን ተመልክቷል፡፡
በመልካም ሥነ-ምግባር የተገነባ ማህበረሰብ፤

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *