ወደ ብልጽግና የምናደርገው ጉዞ ስኬታማ የሚሆነው በውስጣዊ አቅማችን ላይ ከተመሠረተ መሆኑን መረዳት ይገባል። ውስጣዊ አቅማችን ማለትም የሕዝባችን አቅም፣ የሀገራችን ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ሀብት እንዲሁም የአዲሱ ትውልድ የፈጠራ ክህሎት ናቸው፡፡
በአስቸጋሪ ፈተናዎች ውስጥ እያለፍን እንኳን ችግር ተቋቋሚ ኢኮኖሚ ሊኖረን ችሏል፣ የዚህ ዋነኛ ምክንያቱ በመጠኑም ቢሆን ያሉንን ውስጣዊ አቅሞች አሟጠን ለመጠቀም መነሣታችን ነው። ከየትኛውም ወገን የሚሰጠን ድጋፍ በውስጣዊ አቅማችን ላይ ተጨማሪ እንጂ ዋና የዕድገት ምንጭ ሊሆን አይችልም፡፡
ውስጣዊ አቅማችንን ተጠቅመን ወደ ብልጽግና የምናደርገው ጉዞ ከዕንቅፋቶች የጸዳ አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ የኢኮኖሚ አሻጥር፣ ሌብነትና ምርት ስወራ ዋነኞቹ ፈተናዎቻችን ሆነዋል ። ወደ ውጭ መላክ የሚገባውን ምርት መደበቅ፣ ሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ ዝውውርና መሬትን በአሻጥር መውረር በቆራጥነት ፈጣን ርምጃ ልንወስድባቸው የሚገቡ የብልጽግና ዕንቅፋቶች ናቸው።
በቀጣይ ፈተናዎችን የሚሻገር ኢኮኖሚ ለመገንባት እንድንችል ሁለት መልክ ያሉት ትግል ያስፈልገናል ፤ እነዚህም ማጥፋት እና ማልማት ናቸው ብለዋል።
የኢኮኖሚ አሻጥሮችን፣ ሌብነትንና ምርት ስወራን ለማጥፋት የሁላችንንም ወሳኝ ትግል ይፈልጋል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ገቢን የመጨመርና ወጪን በከፍተኛ ሁኔታ የመቀነስ የልማት ትግል ይጠበቅብናል ።
እነዚህ ሁለቱ የትግል መስኮች በራሳችን ፖሊሲና በራሳችን አቅም ማደግ እንድንችል ያስችሉናል ፤ ምክንያቱም የዕድገታችን ቁልፍ በእጃችን ነውና።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልፅግና ፓርቲ

See insights and ads
Boost post
2
Like
Comment
Share
