ኮሚሽነሩ ይህንን ያሉት ኮሚሽኑ ባዘጋጀው የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አመራሮች እና የሚደግፏቸው የመንግስት ተቋማት ስልጠና ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡
ስልጠናውን መስጠት ያስፈለገበት ምክንያት በክልሉ በሚገኙ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚስተዋሉ የሥነ-ምግባር እና የብልሹ አሰራር ድርጊቶችን እና የሚያስከትሉትን ጉዳት በማመላከት፤ ችግሮችን ለመፍታት የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ በዘርፉ የሚጠበቀውን ውጤት ጤናማ ለማድረግ ለማስቻል መሆኑን በመድረኩ ላይ ተጠቅሷል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት በኮሚሽኑ የፊት ለፊት ትምህርትና ስልጠና ባለሙያዎች አቶ ገዛኸኝ የኔው እና አቶ ጥላሁን በሲዞ ሲሆኑ በስልጠናው ከተካተቱት ዋና ዋና ነጥቦች መካከል በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለሥነ-ምግባር ጥሰት፣ ለሙስናና ብልሹ አሰራር የሚያጋልጡ መንስኤዎች እና እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የሚስችሉ የመፍትሔ አቅጣጫዎች መጠቆም ይገኙባቸዋል፡፡
በአሶሳ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ የግል ኮሌጆች የተወጣጡ አመራሮች እና ባለሙያዎች በተሳተፉበት በዚህ ስልጠና ማጠቃለያ ላይ ተሳታፊዎች እንደተናገሩት ስልጠናው በጥናት ላይ ተመስርቶ ወቅቱን ጠብቆ የተሰጠ በመሆኑ በየተቋሞቻቸው ላይ የሚስተዋለውን የሥነ-ምግባር ጉድለቶች እና ብልሹ አሰራሮችን ለማስተካከል የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የዕለቱን መድረክ ሲመሩ የነበሩት አመራሮች አቶ መሐመድ አብዱላዚዝ(የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር) እና አቶ ጌታነ ሰዲ (የህግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ) ትምህርት የሁሉም ሙያዎች መሰረት በመሆኑ በት/ት ተቋማት ላይ የሚመደቡ አመራሮች ብቃትና ዕውቀት በጥንቃቄ ሊታይ ይገባዋል ብለዋል፡፡
የሀሰተኛ የት/ት ማስረጃዎችን በተመለከተ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል፡፡





+3
You, Mengistu Lalo, ታጁ ናሲር and 19 others
1 Comment
3 Shares
Like
Comment
Share
