በተለያዩ ዘርፎች በሚደረጉ የአሰራር ጥናቶች በግብዓትነት በመጠቀም ተቋማት ለሙስናና ብልሹ አሰራር በር የሚከፍቱ አሰራሮችን ሊያሻሽሉ ይገባል፡፡
መንግስቱ ላሎ (የቤ/ጉ/ክ/መ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር)
******************************
(አሶሳ፤ ጥቅምት 23/2015) በተለያዩ ዘርፎች በሚደረጉ የአሰራር ጥናቶች የሚለዩ የአሰራር ክፍተቶችን በግብዓትነት በመጠቀም ተቋማት ለሙስናና ብልሹ አሰራር በር የሚከፍቱ አሰራሮችን ሊያሻሽሉ እንደሚገባ ኮሚሽነር መንግስቱ ላሎ ገለፁ፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሙስናና ብልሹ አሰራርን ቀድሞ መከላከል የሚያስችሉ ተግባራትን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ኮሚሽኑ ከሚሰራቸው የሙስና መከላከል ሥራዎችም አንዱና ዋነኛው የአሰራር ጥናት በማድረግ ለሙስናና ብልሹ አሰራር በር የሚከፍቱ አሰራሮችን በመለየት ምክረ ሃሳብ ማቅረብ ለተፈፃሚነቱም ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ነው፡፡
ባሳለፍነው 2014 የበጀት አመትም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ፤ በግዥና ንብረት አስተዳድር ከሁለት ወር በላይ ባደረገው ጥናት ላይ ከትምህርት ቢሮ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
በውይይቱ ኮሚሽኑ ለሙስናና ብልሹ አሰራር በር የሚከፍቱ ሂደቶችን በተለያዩ ተቋማትና ዘርፎች በማጥናት ምክረ ሃሳቦችን እንደሚያቀርብ ኮሚሽነር መንግስቱ ላሎ ጠቁመዋል፡፡ በክልሉ ትምህርት ቢሮ የግዥና ንብረት አስተዳደር የተገኙ የጥናቱ ግኝቶችንም የሚኖራቸውን ፋይዳ በመረዳት ቢሮውና የተቋማቱ አመራሮችና ባለሙያዎች ሊተገብሯቸው እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
አቶ ቃሲም ኢብራሂም (በክልሉ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ፕሮግራሞች ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ) በበኩላቸው የተጠናው የአሰራር ሥርዓት ጥናት በአሰራር ሂደት ባለማወቅ የሚፈጠሩ የአሰራር ግድፈቶችን የጠቆመና እንዲስተካከሉ እድል የሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ለተፈፃሚነቱም እንደሚሰሩ ገልፀው ኮሚሽኑን አመስግነዋል፡፡
የአሰራር ጥናቱን ያቀረቡት አቶ አለነ ወዲ (በኮሚሽኑ የአሰራር ሥርዓት ጥናት ባለሙያ) በጥናታቸው ያገኞቸውን ለሙስና በር የሚከፍቱ የአሰራር ሂደቶች፣ የመፍትሄ ሃሳቦችና አማራጭ ያሏቸውን መፍትሄዎች አመላክተዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በጥናቱ የተገኙ የአሰራር ክፍተቶች በእርግጥም መስተካከል እንዳለባቸው እንደሚያምኑ ገልፀው ለተፈፃሚነቱ የሚቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል፡፡





You, Admass Tekle, Abera Hambissa and 6 others
2 Comments
1 Share
Like
Comment
Share
