የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በዘጠኝ ወር አፈፃፀሙ ከ36 ሚሊየን ብር በላይ ከምዝበራ ማዳኑን አስታወቀ፡፡

ወቅታዊ መረጃ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በዘጠኝ ወር አፈፃፀሙ ከ36 ሚሊየን ብር በላይ ከምዝበራ ማዳኑን አስታወቀ፡፡

***************

(አሶሳ፤ ግንቦት 21/2015፤ ቤጉ ፀረ-ሙስና) ኮሚሽኑ ከ36, 398,358.93 ከምዝበራ ማዳኑን የ9 ወር አፈፃፀሙን በገመገመበት ወቅት ገልጧል፡፡ ለስራው ውጤታማነትም ከድርጅቶችና ከግለሰቦች 68 ጥቆማዎች መቀበሉ ተመላክቷል፡፡

ተቋሙ የተሰጠው ዋነኛው ተልኮ አስቸኳይ የሙስና መከላከል (ሙስና ከመከሰቱ በፊት የሚመዘበር የመንግስትና የህዝብን ሀብትና ንብረትን ማዳን ነው) ያሉት ኮሚሽነር መንግስቱ ፤ በዚህም ውጤታማ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም ለፀረ-ሙስና ትግሉ ውጤታማነትም የህዝብ የነቃ ተሳትፎ እና የመንግስት ሁለንተናዊ ድጋፍ የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወሰድ ገልፀው፤ ከማህበረሰቡ የሚሰጡ ጥቆማዎችና ከክልሉ መንግስት የሚሰጠው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *