የሙስናን ምንነትና የሚያስከትለውን ዘርፈ ብዙ ጉዳት ከማወቅና ከመረዳት ባሻገር የሙስናና ብልሹ አሰራር ድረጊቶችን ባለመፈጸም በሌሎች ሲፈፀምም አምርሮ በመታገልና በማጋለጥ የተግባር ሰው መሆን፤ በተጨማሪም ሙስናን ትርጉም ባለው መንገድ ለመታገል ወሳኝ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
የዘንድሮው የአለም የፀረ-ሙስና ቀንም በሃገራችን ለ18ኛ ጊዜ በአለም ደግሞ ለ19ኛ ጊዜ ህዳር 30 በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በድምቀት ይከበራል፡፡ የበዓሉ መሪ ቃልም “ሙስናን መታገል በተግባር!” የሚል ሁኗል፡፡
