የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት የፀረ-ሙስና ቀን በዓል አከበረ፡፡
**********************
የቤ/ጉ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች በሥነ-ምግባር የታነፀ አመራር ከሙስና ለፀዳች ኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ18ኛ በሀገራችን ለ17ኛ ጊዜ የሚከበረዉን የፀረ-ሙስና ቀን የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ም/ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ነጂመድን አልመሃዲ በገተኙበት ዳኞችና ሠራተኞች በድምቀት አከበሩ ፡፡
በዕለቱ በተቋሙ የተሻለ የሥራ አፈጻጸም ላስመዘገቡና በሥነ-ምግባራቸዉ ከፍተኛ ዉጤት ያመጡ ባለሙያዎችና ሰራተኞች ከክቡር አቶ ነጂመድን አልመሃዲ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
