በሙስና ምክኒያት 2.2 ቢሊዮን ብር የህዝብና የሀገር ሀብት ለብክነት መዳረጉን ሀገራዊ የፀረ ሙስና ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ተመስገን ጥሩነህ አስታወቁ:: *****************************

ወቅታዊ መረጃ
የብሄራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት እስካሁን በተከናወኑ የሙስና ተግባር 759 የሙስና ወንጀሎች ከህብረተሰቡ ጥቆማ የቀረበ ሲሆን፤ ከተጠቆሙት መካከል 175 የሙስና ወንጀሎች በመለየት ምርመራ እየተደረገበት እንደሆ ገልፀዋል። ከዚህ ውስጥ በ81 ላይ ክስ በመመስረት ተጠያቂነት እያደረጉ መሆኑን ጠቁመው። 2.2 ቢሊዮን ብር የህዝብና የመንግስት ሀብት ለብክነት መዳረጉን የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገልፀዋል።
640 የሚሆኑ ግለሰቦች ክስ በመመስረት ግለሰቦች ተጠያቂ እንደሆነ ገልፀዋል።
በሌላ በኩል 25,885 ካ.ሜ በምርመራ የሙስና ወንጀል ተፈፅሞ መገኘቱን ጠቁመዋል። የክልሎች ሲጨመር ምን ያክል እንደሚሆን ለመረዳት ይቻላል ሲሉ ተደምጠዋል።
የሙስና ወንጀልን ለመቀነስ የትስሰር ገመድን መበጠስ ይገባል ያሉ ሲሆን፤ ችግሩ የሀገራችን የፖሊሲ የማስፈፀም አቅም የሚያዳክም ነው ብለዋል። በመሆኑም ችግሩን ዳር ለማድረስ ህብረተሰቡ ከፀረ-ሙስና ኮሚቴው ጎን በመቆምና የተጀመረውን ጥቆማ የመስጠት ተግባር አጠናክረው መቀጠል እንዳለበት የኮሚቴው ሰብሳቢና የኢፈድሪ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ መልክት አስተላልፈዋል።
ውይይቱ በፌደራል፣ በክልል እና በከተማ መስተዳድር የተቋቋመው የፀረ-ሙስና አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ነው እየተካሄደ ያለው።
መድረኩ እስካሁን የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት የጋራ ግምገማ ለማካሄድና የቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ያለመ መሆኑም ተገልጿል።
የፌዴራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *