የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች የሙስና መከላከል ስራዎችን ውጤታማነት ለማሳደግ በሚያስችለው የ2015 የበጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ተወያዩ፡፡

ወቅታዊ መረጃ
(አሶሳ፤ ሐምሌ 14 /2014) የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች እና ባለሙያዎች በ2015 የበጀት ዓመት የሙስና መከላከል ሥራዎችን በተሻለ መልኩ ለመፈፀም ይረዳ ዘንድ በበጀት አመቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ዕቅድ ቀርቦ ሁለት ቀናት የወሰደ ውይይት በኮሚሽነሩ ጽ/ቤት ተደርጓበታል፡፡
ኮሚሽኑ በበጀት አመቱ አስቸኳይ የሙስና መከላከል ስራዎች (በስነ-ምግባር እሴቶች ግንባታ ፣ የአውታሮች አደረጃጀትና የአሰራር ጥናት) ፣ የሀብት ምዝገባ እና ማጣራት እንዲሁም የሙስናና ብልሹ አሰራ ጥቆማዎች እና ሌሎች የሙስና መከላከል እስትራቴጅዎችን ውጤታማነት ማሳደግና ማሻሻል ላይ ትኩረቱን አድርጎ እንደሚሰራ በቀረበው የ2015 ዕቅድ ተመላክቷል፡፡
የኮሚሽኑን ሰፊ ዕቅድ ለመፈፀም የበጀትና የሎጀስቲክ ዕጥረት ሊፈትን እንደሚችል በውይይቱ የተነሳ ሲሆን በክልሉ ሙስናና ብልሹ አሰራር የልማት እና የዕድገት እንቅፋት ከማይሆንበትን ደረጃ ለማድረስ ኮሚሽኑ በቂ በጀትና እና ሎጅስቲክ ሊመደብለት እንደሚገባ በውይይቱ ሃሳብ ተሰጥቷል፡፡
በሌላ በኩል ከመንግስት በጀት በተጨማሪ ሌሎች አማራጮችን ማየት እና መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመቀራረብ መስራት እንደሚገባ በዚህም አበረታች ውጤቶች መኖራቸው በአመራሩ ተጠቁሟል፡፡
በዚሁ ውይይት የኮሚሽኑን ማሻሻያ አዋጅ ለማፅደቅ በክልሉ መንግስት በኩል በጎ ምላሽ መገኘቱን ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚነሳውን የኮሚሽኑን አደረጃጀት በማስተካከል በሙስና መከላከሉ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ መልካም አጋጣሚ መሆኑ ተብራርቷል፡፡
ኮሚሽነር መንግስቱ ላሎ በተያዘው የበጀት አመት አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ ሁሉም የኮሚሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች ሙሉ አቅማቸውን በመጠቀም እንዲረባረቡ አሳስበዋል፡፡
በተጠናቀቀው የበጀት አመት ኮሚሽኑ ከ21 ሚሊዬን ብር በላይ ከምዝበራ በማዳን ወደ መንግስት ካዝና እንደሚለስና ለህዝብና ለመንግስት ጥቅም እንዲውል ማድረጉን መዘገባችን የሚታወሰ ነው፡፡
የኮሚሽኑን የ2015 የበጀት አመት እቅድ ያቀረቡት አቶ ቶሎሳ ጅግልዱ (በኮሚሽኑ ዕቅድ ባለሙያ) ናቸው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *