የተማሪዎች የስነ-ምግባር ክበባት የተማሪዎችን ባህሪ በመለወጥ ረገድ ውጤታማ ናቸው፡፡ወ/ሮ አሚናት ሐሰን (በኩሙሩክ ወረዳ የማህበራዊ ክላስተር የስነ-ምግባር መከታተያ ክፍል)
*************************
በኩሙሩክ ወረዳ በት/ቤቶች የተቋቋሙ የተማሪዎች የሥነ-ምግባር ክበባት የተማሪዎችን ባህሪ በማስተካከል ረገድ ውጤታማ መሆናቸው ተገለፀ፡፡
ከዝግጅት ክፍላችን ጋር ቆይታ ያደረጉት ወ/ሮ አሚናት ሐሰን (በኩሙሩክ ወረዳ የማህበራዊ ክላስተር የስነ-ምግባር መከታተያ ክፍል) እንደገለፁት በወረዳው ከሚገኙ 19 ት/ቤቶች በ18 ክበቡ መቋቋሙና ወደ ስራ መገባቱን ነግረውናል፡፡
በአዲስ የተቋቋመው የተማሪዎች የሥነ-ምግባር ክበብ ተማሪዎች ኩረጃን እና ሌብነትን እንዲፀየፉ፣ ከመምህራኖቻቸው ጋር መልካም ግንኙነት እንዲኖራቸው እና ተማሪዎች መብትና ግዴታቸውን አውቀው እንዲተገብሩ ማስቻሉን ገልፀዋል፡፡
ወ/ሮ አሚናት ሐሰን አክለውም የስነ-ምግባር ክበባቱ ከዚህ በተሻለ ውጤታማ እንዲሆኑ ከወረዳ አስተዳደሩ ጋር በመነጋገር የክትትልና ድጋፍ ስራዎች እንደሚሰሩ ጠቁመዋል፡፡
