አትስረቅ…!አትስረቅ…!አትስረቅ
************************
የቤኒሻንጉል ጉ/ክ/መ/የስነምግባር ና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን በአሶሳ ዞን ስር በሚገኙ የሐይማኖት ተቋማት የጸረ-መስና ንቅናቄ ጥምረት የ2014 የመጀመሪያው አጋማሽ አፈጻጸም ዙሪያ በሆሞሻ ውይይት
ተካሄደ ።
በወይይቱ ላይ በአሶሳ ዞን ስር ከሚገኙ ወረዳዎች የመጡ የሐይማኖት አባቶችና የስነምግባር መከታተያ ክፋል ባለሙያዎች ተሳታፊ ሁነዋል።
በውይይቱ ላይ በሁሉም የእምነት አስተምህሮ መስረቅ ሀጥያት መሆኑን ያነሱት አባቶች ለዚህም በተከታዮቻቸው ዘንድ እንዲ አይነቱ ነውር እንዳይከሰት እየሰሩ መሆናቸውንና ይህንንም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በውይይቱ አረጋግጠዋል፡፡ አያይዘውም ህፃናት ላይ ከፍተኛ ስራ መሰራ እንዳለበት ለዚህ ደግሞ ከወላጅ ጀምሮ ሀሉም የድርሻውን መወጣት እንደሚገባ ተገልጿል ።
የቤ/ጉ/ክ/የስነ-ምግባርና ጸረ-መስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ መንግስቱ ላሎ የሐይማኖት አባቶች በየቤተ-እምነት እና በአምልኮ ስፈራ ተከታዮቻቸውን በመልካም ስነ-ምግባር፣ በሞራል እሴቶች እና በመልካም ሐይማኖታዊ አስተምህሮ በማነጽ ጠቃሚ የሆኑ መልካም እሴቶችና ባህሎቻችን እንዲጎለብት ከማድረግ አንጻር ሰማያዊ እና ምድራዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
