ሙስና የሀገርን ዕድገት እና የህዝቦችን ተጠቃሚነት የሚጎዳ በመሆኑ አገልጋዮች ከብልሹ አሰራርና ሙስና ነጻ ሁነው አገልግሎት መስጠት ይገባቸዋል፡፡ አቶ ኤሊያስ ወዲሻ (በኮሚሽኑ የሐብት ማስመዝገብና ማሳወቅ ዳይሬክተር)

ወቅታዊ መረጃ

(ግልገል በለስ ህዳር 10/2017 ዓ.ም፤ የቤጉክ የሥ/ፀረ – ሙስና ኮሚሽን)  ሙስና የሀገርን ዕድገት እና የህዝቦችን ተጣቃሚነት  የሚጎዳ  በመሆኑ አገልጋዮች  ከብልሹ አሰራና ሙስና ነጻ ሁነው አገልግሎት መስጠት   እንደሚገባቸው በኮሚሽኑ የሐብት ማስመዝገብና ማሳወቅ ዳይሬክተሩ አቶ ኤሊያስ ወዲሻ ገለፁ፡፡

ኮሚሽኑ ከግልገል በለስ  ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር የሥራ ስነ-ምግባርና ሙስናና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ረገድ የባለድርሻ አካላት ሚና በሚሉ ሁለት ሰነዶች   በከተማ አስተዳደሩ ለሚሰሩ አመራሮችና የሥራ ኃላፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በስልጠና መድረኩም አቶ ኤሊያስ ወዲሻ አገልጋዮች የሚሰጡት  አገልግሎት በህግ አግባብ ያለ እጅ መንሻ ሊሰጡ  እንደሚገባ   በዚህ ልክ መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

በዚህ መድረክ ግልፅነት የሚሹ ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች የተነሱ ሲሆን  መድረኩን የመሩት በኮሚሽኑ የሐብት ምዝገባ ዳይሬክተር አቶ ኤሊያስ ወዲሻ እና የከተማ አስተዳደሩ ተወካይ ከንቲባ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የግንዛቤ ስልጠናውን የሠጡት   በኮሚሽኑ የሥልጠና ባለሙያ አቶ ንጋቱ ጌታሁን  ናቸው፡፡

መሰል የግንዛቤ ስልጠናዎች ከሳምንት በፊት ለባምባሲ ከተማ አስተዳደርም በተመሳሳይ ይዘቶች ለሚመለከታው አካላት ግንዛቤ መፍጠር መቻሉን መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡

 

በመልካም ሥነ-ምግባር የተገነባ ማህበረሰብ፤

 

ለጥቆማ – www.bgrseacc.gov.et

ፌስ ቡክ – https://web.facebook.com/bgrseacc

ቴሌግራም – https://t.me/bgrseaccpr

ዩቲዩብ – https://www.youtube.com/channel/UCLXoTV-dWDw1z7yNAPnbYYQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *