በዓለማቀፍ ለ21ኛ፤ በሃገር-አቀፍ ለ20ኛ ጊዜ «ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል የነገ ስብዕናን ይገነባል!» በሚል መሪ ቃል በመላው ክልሉ በሚገኙ የመንግስት ተቋማት ሲከበር የቆየው የፀረ-ሙስና ቀን ማጠቃለያ ፓናል ውይይት ተካሄደ፡፡
በዕለቱ የክብር እንግዳ በመሆን መድረኩ ላይ ተገኝተው በፀረ-ሙስና ትግሉ የክልሉን መንግስት አቋም ያብራሩት ክቡር ም/ር/መስ አቶ ጌታሁን አብዲሳ የፀረ-ሙስና ትግሉ ቀጣይነት ባለው መልኩ ሁሉን ባለድርሻ አካላት ባሳተፈ መልኩ መልካም ስብዕናን በመቅረጽ፤ ሙስናን በመከላከል ረገድ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል፡፡
የክልሉ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር መንግስቱ ላሎ በመድረኩ መክፍቻ ላይ ዕለቱን ማክበር ያስፈለገበት ዓላማ የሙስና ወንጀል ድንበር ዘለል በመሆኑ ሀገራት በተናጥል ከሚያደርጉት የፀረ-ሙስና ትግል በተጨማሪ በጋራ በተቀናጀ መልኩ ሙስናን ለመከላከል የሚያስችላቸውን ኮንቬንሽን ያጸደቁበት ቀንን ለማስታወስ መሆኑን ጠቁመው ታላላቅ ሀገራዊ የልማት ህልሞቻችንን ለማሳካትና ሁለንተናዊ ዕድገቷ የተረጋገጠ ኢትዮጵያን ለመፍጠር ወጣቱን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በማጠቃለያ መድረኩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፤ ባለሙያዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ተሳትፈዋል፡፡





+6
See insights and ads
Boost post
All reactions:
You, ቦሌ ወረዳ 06 ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና Anti Corruption and 8 others
