አገር ዓቀፍ የሥነ ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች የትስስረ ጉባዔ ተካሄደ

ወቅታዊ መረጃ

የፌደራል፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደር የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነሮች እና ም/ኮሚሽነሮች እንዲሁም የኮሚሽኑ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት 12ኛው አገርዓቀፍ የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች የትስስር ጉባኤ ተካሄዷል።

በጉባኤው የ15ቱም ኮሚሽኖች በአገርዓቀፍ የትውልድ የሥነምግባር ግንባታና የፀረ-ሙስና ትግል ባለፉት 6 ወራት የተገኙ ውጤቶች፣ ጥንካሬዎች፣ ድክመቶች፣ ተግዳሮቶች፣ መልካም ተሞክሮዎች እና ቀጣይ አገራዊ የትኩረት ጉዳዮች ቀርበው ምክክር ተካሄዶበታል።

በትስስር ጉባኤው ንግግር ያደረጉት የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ፒኤችዲ) የትውልድ የሥነምግባር ግንባታ ሥራን ውጤታማ ለማድረግ ቤተሰብ ላይ ትኩረት አድርገን መስራት አለብን ብለዋል።

የተቋማት መሪዎችም የፀረ-ሙስና ትግሉ ላይ ባለቤት በመሆን ተቋማቸውን ከብልሹ አሰራር ነፃ ማድረግ እንዳለባቸው ተናግዋል።

የኮሚሽኑ የሙስና መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ክቡር እሸቴ አስፋው በበኩላቸው በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን ትኩረት ሰጥተን መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በተለይ ከመንጃ ፍቃድ አሰጣጥ፣ ከግብር አሰባሰብ፣ ከነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን መከላከል እንደሚገባ ተናግረዋል።

ም/ኮሚሽነሩ አክለውም በተቋማት ላይ ያሉ የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎችንም አቅም በመገንባት በፀረ-ሙስና ትግሉ ላይ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ማድረግ አለብን ብለዋል።

የኮሚሽኑ የሥነምግባር ግንባታ ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ክቡር ፍቃዱ ሰቦቃ በበኩላቸው የሥነምግባር ግንባታ እና ሙስና መከላከል ተልእኮ በአግባቡ መወጣት ይገባል ብለዋል።

ምክትል ኮሚሽነሩ አክለውም የሁላችንም ተልዕኮ በሥነምግባሩ የታነፀ፣ ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን የሚፀየፍ እንዲሁም ሙስናን መሸከም የማይችል ብሎም አምርሮ የሚጠላ ዜጋና ትውልድ ማፍራት ይገባል ብለዋል።

በአገርዓቀፍ ደረጃ ያሉ የሥነምግባር ክበባትን በማጠናከር ለሥነምግባር ግንባታና ለፀረ-ሙስና ትግሉ አጋዥ እንዲሆኑ ማድረግ አለብን ብለዋል።

በጉባኤው ማጠቃለያ አገራዊ የፀረ-ሙስና ትግሉ ወደተሻለ ምዕራፍ ለማሻገር ትስስሩና ትብብሩ ሁሉንአቀፍ እና የተቀናጀ ለማድረግ የሚያስችል የጋራ አቅጣጫ በማስቀመጥ የአቋም መግለጫ ተሰጥቷል።

Federal Ethics and Anti-Corruption Commission

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *