የወጣቶች ፤ የመልካም ሥነ-ምግባር ባለቤት መሆን ፤ በዘላቂ ሕይወታቸው ደስተኛና የተሻለ የኑሮ ዘይቤ እንዲኖሩ ያስችላል – አቶ ንጋቱ ጌታሁን

ወቅታዊ መረጃ

ለአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተማሪዎች ወጣትነትና ሥነ-ምግባር በሚል ርዕስ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የኮሚሽኑ የፊት ለፊት የሥነ-ምግባር ትምህርትና ስልጠና ባለሙያ አቶ ንጋቱ ጌታሁን የሥልጠናው ዓላማ ወጣቱ መልካምና እኩይ እሴቶችን ለይቶ ትክክለኛውን መንገድ ማሳየት፤ መልካም ስነ-ምግባርን ለሌሎች ማሻገር መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የወጣቶች የመልካም ሥነ-ምግባር ባለቤት መሆንም፤ በዘላቂ ሕይወታቸው ደስተኛና የተሻለ የኑሮ ዘይቤ ለመኖር እንደሚያስችላቸው ነው፤ ባለሙያው ያስገነዘቡት፡፡

ሥነ-ምግባር፤ ለሚያጋጥሙ ችግሮች ምህረት ሰጭ መመሪያ ነው ያሉት አቶ ንጋቱ ወጣቶች የተራማጅ አስተሳሰብ ባለቤት መሆን እንደሚጠበቅባቸው አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡

ይህም ተማሪዎች ከኮሌጅ ህይወታቸው ሲወጡ በሚኖራቸው ሃገርን መውደድ፤ ከሙስናና ብልሹ አሰራር የፀዳ አገልግሎት በመሰጥት እንደሚለካ ነው ባለሙያው ያብራሩት፡፡

ለወጣቶች የሥነ-ምግባር ግንባታ ልዩ ትኩረት የተሰጠውም፤ ወጣቶች ያላቸው ከፍተኛ ቁጥርና በማህበራዊ ጉዳይ ያላቸው ተሳትፎ እንዲሁም ሙስናና ብልሹ አሰራር ከሌላው የህበረተሰብ ክፍል በተለየ ሁኔታ ወጣቱን የሚጎዳ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የወጣቱን ሥነ-ምግባር ማሻሻል ካልተቻለም እንደ ሃገር የሚኖረው ጫና ከፍተኛ መሆኑን አቶ ንጋቱ ጌታሁን ጠቁመዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *