ኮሚሽኑ ላለፉት ዘጠኝ ወራት የኮሚሽኑን የፀረ-ሙስና ትግሉ ያሳካሉ ብሎ ባቀዳቸው የትምህርትና ስልጠና፣ የሐብት ምዝገባ፣ አውታሮች፣ የአሰራር ጥናት እና ተያያዥ ዘርፎች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በሂደቱ የተገኘ አፈፃፀሙን ገምግሞል፡፡
ተቋሙ የፀረ-ሙስና ትግሉን ውጤታማ ለማድረግ በሄደባቸው እርቀቶችም የበጀት (የጥሬ ገንዘብ እጥረት) ፈተና መሆኑን ኮሚሽነር ከማል ሀሰን ገልፀዋል፡፡ በቀጣይ ቀሪ ስረዎችን ለመስራትም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ነው ያስታወቁት፡፡
በሂደቱም ተመጣጣኝ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን የኮሚሽኑ የእቅድ ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክተሩ አቶ አብርሐም ፋሲል አመላክተዋል፡፡

