
በተያዘው የበጀት ዓመት የኮሚሽኑን የሙስና መከላከል ስራዎች ውጤታማነት ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ ኮሚሽነር ከማል ሃሰን ገለፁ፡፡ ለውጤታማነቱም የኮሚሽኑን የስራ መሳሪያዎች ለማስተካከል ጥረት መደረጉንና የሰው ኃይል አደረጃጀቱን ለመከለስ መሞከሩን ጠቁመዋል፡፡
ኮሚሽነሩ ይህን ያሉት የተቋሙ የአንድ ዓመት እቅድ በአስተዳደር አካላት በተገመገመበት ወቅት ነው፡፡
ተቋሙ በአዋጅ የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት ከወዲሁ ግልፅ እቅድ ማቀዱን የገለፁት ኃላፊው፤ በእቅዱ የተቋሙን የሙስናና ብልሹ አሰራር መከላከል ውጤታማነት የሚያሳድጉ ተግባራት ትልቁን ድርሻ የሚወስዱ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡
አክለውም የኮሚሽኑ አስተዳደር አካላት በቀጣይ ሊሰሩ በሚችሉ የአስቸኳይ ሙስና መከላከል፣ የትምህርትና ስልጠና የአሰራር ጥናት፣ የሐብት ማስመዝገብና ማሳወቅ፣ የአውታሮች አደረጃጀትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ አመርቂ ስራ ለመስራት ከወዲሁ እርብርብ እንዲደረግ ነው፤ የሥራ አቅጣጫ ያስቀመጡት፡፡
የኮሚሽኑን የአንድ አመት እቅድ ´ለማኔጅመንቱ´ ያቀረቡት የተቋሙ የእቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ባለሙያ አቶ ቶሎሳ ጅግልዱ ናቸው፡፡
