ሕዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማትና የመልካም አስተዳድር ዕቅዶች ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ ነው – ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን

ወቅታዊ መረጃ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

 

‎‎የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በመድረኩ ማስጀመሪያ፤ በ2018 የበጀት ዓመት ሕዝብን  ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማትና የመልካም አስተዳድር ዕቅዶች ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

‎በመጀመሪያ ሩብ ዓመት በመኸር እርሻ፣ በማዕድን፣ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ በንቅናቄ ሥራዎች የተሻለ አፈጻጸም መመዝገቡንም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል፡፡

 

‎የአፈጻጸም ግምገማው በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የታዩ ጥሩ አፈጻጸሞችን በላቀ ሁኔታ ለማስቀጠል፣ ውስንነቶችን  ለማረም እና በቀጣይ ለሚከናወኑ ተግባራት አቅጣጫ ለማስቀመጥ የሚያግዝ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልፀዋል፡፡

‎‎

 

‎የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ቃሲም ኢብራሂም፣ ክልሉ በበጀት ዓመቱ የተለዩ 12 ዋና ዋና የትኩረት መስኮችን ለመፈጸም እየሠራ መሆኑን ጠቁመው፣ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በተለያዩ ዘርፎች አበረታች አፈጻጸም መመዝገቡን አብራርተዋል፡፡

 

 

‎የክልሉ የአስፈጻሚ አካላት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *