̎ለህዝብ ፍላጎትና ጥያቄ በቂ መልስ ለመስጠት አበክሮ  መስራት ያስፈልጋል ̎  የተከበሩ አቶ መለሰ ኪዊ (የቤሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ም/አፈ -ጉባኤ) 

ወቅታዊ መረጃ

አሶሳ፣ ሚያዚያ29 /2017 ዓ.ም (የቤ/ጉ/ክ/መ/ የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን)  የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን፣ የክልሉ  ዋና ኦዲት እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት የብልፅግና ፓርቲ አባላትና አመራሮች የመሐሉ ዘመን በሚል ርዕስ በተዘጋጀ  ሰነድ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

 

ሰነዱን ለአባላቱ ያቀረቡት የቤሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ም/አፈ -ጉባኤ የተከበሩ  አቶ መለሰ ኪዊ አሁንም ያልተፈቱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች  እና መልስ ያላገኙ የህዝብ ጥያቄዎች መኖራቸውን ገልፀው ፤ አመራሩና  አባላቱ ለህዝብ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት በሚሰሩባቸው  ተቋማት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ  በመወጣትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት  የአንበሳውን ድርሻ እንዲወጡ  ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 

በዚህ መድረክ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫና የርብርብ  መስኮች በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን፤ የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎችን በመስራት የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *