የቤኒሻነንጉል ጉሙዝ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የኢንስፔክሽንና ቁጥጥር ኮሚሽን በክልሉ በተዋረድ ከተደራጁ የኢንስፔክሽንና ቁጥጥር መዋቅሮች ጋር የኢንስፔክሽኑን የዘጠኝ ወር አፈፃፀምና ተያያዥ ጉዳዮች በሚመለከት ውይይት እያደረገ ነው፡፡
የኢንስፔክሽን ኮሚሽኑ በተለይ በመንግስት ተቋማት የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ማስተካከል በሚቻልበት ሁኔታ ሰፊ ውይይት እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የኢንስፕፔክሽንና ቁጥጥር ኮሚሽን ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው የሚታወስ ነው፡፡
ዝርዝር ጉዳዮችን ይዘን እንመለሳለን፤

