የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን እና የክልሉ ወሳኝ ኩነት ቢሮ በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ፡፡
ሁለቱ ተቋማት በትውልድ ሥነ-ምግባር ላይ መስራታቸው ተልዕኳቸውን በጋራ ለማሳከት መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር መሆኑ በውይይቱ ተገልፆል፡፡
የሥነ-ምግባር ግንባታ ውጤታማነትን ለማረጋገጥም ዜጋው ከስነ-ምግባር ብልሽት እና ከብልሹ አሰራሮች እራሱን እንዲያርቅ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላትን በመያዝ በትኩረት እንደሚሰራ ኮሚሽነር ከማል ሃሰን ጠቁመዋል፡፡
ሁለቱ ተቋማት በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው የሚታወስ ነው፡፡


