በመተከል ዞን ስር ለሚሰሩ የመከታተያ ክፍል ባለሙያዎች ስልጠና ሊሰጥ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታወቀ።
ስልጠናው በስራ ላይ ስነ ምግባር ፣ በሀብት ማስመዝገብና ማሳወቅና ተያያዥ ጉዳዮች እንዲሁም የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያዎች ተግባርና ኃላፊነት ላይ ትኩረቱን አድርጎል።
የመድረኩ አላማም የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያዎች የተሰጣቸውን ትውልድን በመልካም ስነ ምግባር የማነጽና ሙስናና ብልሹ አሰራርን የመከላከል ሚና ማሳደግ መሆኑን ኮሚሽነር ከማል ሃሰን ተናግረዋል።
ሥልጠናው በግልገል በለስ ከተማ የሚሰጥ ሲሆን ከነገ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

