ወጣቶች እራሳቸውን በሥነ-ምግባር በመግራት ህይወታቸውን በምክንያታዊነት መምራት ይገባቸዋል – አቶ  አወቀ ገ/መስቀል

ወቅታዊ መረጃ

የተማሪዎችን ስብዕና መገንባት አላማ ያደረገ ሥልጠና ለብራይት ሜዲካል ኮሌጅ አሶሳ ካምፓስ ተማሪዎች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

 

ወጣቶች እራሳቸውን በሥነ-ምግባር በመግራት እና እራሳቸውን በመቆጣጠር ሕይወታቸውን በምክንያታዊነት መምራት እንደሚጠበቅባቸው የኮሚሽኑ የፊት ለፊት የሥነ-ምግባር ትምህርትና ስልጠና ባለሙያ አቶ አወቀ ገ/መስቀል ትምህርቱን  በሰጡበት ወቅት ተናግረዋል፡፡

 

የህክምና ሙያ በጥብቅ ሥነ-ምግባር መመራት አለበት ያሉት   አቶ አወቀ ተማሪዎች  በቀጣይ ወደ ስራው  አለም በሚሰማሩበት ወቅትም ማህበረሰብን በመልካም ስነ-ምግባር ማገልገል እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመዋል፡፡

 

አያይዘውም ወጣቱ ከማህበረሰብ ባህልና ወግ ካፈነገጡ ልማዶች  እራሳቸውን በመጠበቅ  ለዓላማቸው እንዲተጉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

 

በመድረኩ ከ300 በላይ ተማሪዎች  ሥልጠናውን ወስደዋል፡፡

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *