
ኮሚሽኑ በክልሉ መንግስት ለ2018 እቅድ ማስፈፀሚያ የተሰጠውን ውስን በጀት በቁጠባና ለታለመለት ዓላማ በማዋል ውጤታማ የሙስና መከላከል ስራዎችን አበክሮ እንደሚሰራ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ከማል ሃሰን ገለፁ፡፡
አጠቃላይ የተቋሙን መደበኛና ፕሮግራም በጀት በሚመለከት ከኮሚሽኑ አመራሮችና የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ያደረጉት ኃላፊው፤ የበጀት አጠቃቀምን በደንብና መመሪያ በመምራት አፈፃፀምን ማሳደግ እንደሚገባም ነው ያስገነዘቡት ፡፡
የተቋሙን የማስፈፀሚ በጀት ያቀረቡት የኮሚሽኑ የዕቅድ ዝግጅት ባለሙያ አቶ ቶሎሳ ጅግልዱ ናቸው፡፡
